ኤርምያስ 30:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ከእርሱም ዘንድ የምስጋናና የዘፋኞች የሐሤት ድምፅ ይወጣል፤ እኔም አበዛቸዋለሁ አያንሱምም፥ እኔም አስከብራቸዋለሁ ታናሽም አይሆኑም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ከእነርሱም የምስጋና መዝሙር፣ የእልልታ ድምፅ ይሰማል። እኔ አበዛቸዋለሁ፤ ቍጥራቸውም አይቀንስም፣ አከብራቸዋለሁ፤ የተናቁም አይሆኑም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 በዚያም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ የምስጋና መዝሙር ይዘምራሉ፤ በደስታም እልል ይላሉ፤ አበዛቸዋለሁ እንጂ ቊጥራቸው አይቀንስም፤ ክብር እንዲኖራቸው አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ አይናቁም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ከእርሱም ዘንድ የምስጋናና የዘፈን ድምፅ ይወጣል፤ እኔም አበዛቸዋለሁ፤ አያንሱምም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ከእርሱም ዘንድ የምስጋናና የዘፋኞች ድምፅ ይወጣል፥ እኔም አበዛቸዋለሁ አያንሱምም፥ እኔም አከብራቸዋለሁ ታናሽም አይሆኑም። See the chapter |