ኤርምያስ 3:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 በእውነት ኮረብቶች ሐሰት ናቸው፥ በተራሮችም ላይ ሁከት ነው፤ በእውነት የእስራኤል መዳን በአምላካችን በጌታ ነው።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 በርግጥ በኰረብቶች ላይ፣ እንዲሁም በተራሮች ላይ፣ ሆ! ብለን መውጣታችን መታለል ነው፤ በርግጥ የእስራኤል መዳን፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 በኮረብቶች ራስ ላይ ቅጥ ያጣ የባዕድ አምልኮ ፈንጠዝያ መፈጸማችን ምንም አልጠቀመንም፤ ለእስራኤል መዳን የሚገኘው ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ብቻ ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 በእውነት የተራሮች ኀይል፥ የኮረብቶችም ኀይል ሐሰት ነው፤ ነገር ግን የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 በእውነት የኮረብቶችና የተራሮች ፍጅት ከንቱ ናት፥ በእውነት የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ነው። See the chapter |