ኤርምያስ 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 የእስራኤል ልጆች መንገዳቸውን አጣምመዋልና፥ አምላካቸውንም ጌታን ረስተዋልና በተራቈቱ ኮረብቶች ላይ የልመናቸው የለቅሶ ድምፅ ተሰማ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት፣ መንገዳቸውን አጣመዋልና፣ የእስራኤል ሕዝብ ጩኸት፣ አሳዛኝ ልቅሶ ባድማ ከሆኑት ኰረብቶች ተሰማ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ልምላሜ በሌለባቸው ኰረብቶች ራስ ላይ ድምፅ ይሰማል፤ ይህም ድምፅ፥ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት ኃጢአት ሲሠሩ ኖረው፥ አሁን በመጸጸት የሚያሰሙት የለቅሶና የልመና ድምፅ ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 የእስራኤል ልጆች በመንገዳቸው ዐምጸዋልና፥ ቅዱስ አምላካቸውንም ረስተዋልና ከብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ፤ የእስራኤል ልጆች ልቅሶና ጩኸትም ተሰማ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 የእስራኤል ልጆች መንገዳቸውን አጣምመዋልና፥ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተዋልና በወናዎች ኮረብቶች ላይ የልመናቸውና ልቅሶአቸው ድምፅ ተሰማ። See the chapter |