Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 29:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ተጋቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ ሴቶች ልጆቻችሁንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አጋቡ፥ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፤ በዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አግብታችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ውለዱ፤ ወንዶች ልጆቻችሁንና ሴቶች ልጆቻችሁን አጋቡ፤ እነርሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ይውለዱ፤ ቍጥራችሁም በዚያ ምድር ይብዛ እንጂ አይነስ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እየተጋባችሁ ልጆችን ውለዱ፤ ልጆቻችሁም በተራቸው እየተጋቡ ልጆችን ይውለዱ፤ ቊጥራችሁ ይብዛ እንጂ አይቀንስ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጋቡ፤ እነ​ር​ሱም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችን ይው​ለዱ፤ ከዚ​ያም ተባዙ፤ ጥቂ​ቶ​ችም አት​ሁኑ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ተጋቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፥ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፥ ከዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 29:6
16 Cross References  

እርሱም ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት። ሴቶች ልጆቹንም ከጐሣው ውጭ ለሆኑ ሰዎች ዳራቸው፤ ጐሣው ውጭ የሆኑ ሠላሳ ልጃገረዶች አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋር አጋባቸው። ኢብጻን በእስራኤል ላይ ሰባት ዓመት ፈራጅ ሆነ።


ላባም፦ “ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጣት ይሻላል፥ ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለ።


ርብቃ እነኋት በፊትህ ናት፥ ይዘሃት ሂድ፥ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ለጌታህም ልጅ ሚስት ትሁን።”


በፋራን ምድረ በዳም ተቀመጠ፥ እናቱም ከምድረ ግብጽ ሚስት ወሰደችለት።


እንግዲህ ወጣት መበለታት እንዲያገቡ፥ ልጆችንም እንዲወልዱ፥ እያንዳንዳቸውም ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስተዳድሩ እፈቅዳለሁ፤ በዚህም ተቃዋሚ የሚሳደብበትን ምንም ዓይነት ሰበብ እንዳይሰጡት ነው፤


እንደተመለሰም አባቱንና እናቱን፥ “በቲምና አንዲት ወጣት ፍልስጥኤማዊት አይቻለሁና አሁኑኑ አጋቡኝ” አላቸው።


ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፥ “ይህችን ልጅ አጋባኝ” አለው።


እናንተ ፍሬያማ ሆናችሁ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ።”


ርብቃንም መረቁአትና፦ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፥ ዘርሽም የጠላቶችን ደጅ ይውረስ” አሉአት።


እናንተ ሂዱ፥ ከምታገኙበትም ስፍራ ገለባ ሰብስቡ፤ ከሥራችሁ ግን ምንም አይጉደል።’”


Follow us:

Advertisements


Advertisements