Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 29:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እርሱ፦ “ለረጅም ጊዜ በምርኮ ስለምትቆዩ ቤቶችን ሠርታችሁ ተቀመጡ፥ አታክልትንም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ” ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢሎን ልኮአልና።’ ”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ይህ ሰው፣ “የምርኮው ጊዜ ረዥም ስለ ሆነ፣ ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፤ አትክልትም ተክላችሁ ፍሬውን ብሉ” በማለት ወደ ባቢሎን መልእክት ልኮብናል።’ ”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እርሱ እንዳይናገር መከልከል አለበት፤ ምክንያቱም ወደ ባቢሎን ተማርከው የተወሰዱት ሕዝብ ገና ብዙ ዘመን መኖር እንዳለባቸው በመቊጠር ‘ቤት ሠርታችሁ ተደላድላችሁ ኑሩ፤ አትክልት ትከሉ፤ ፍሬውንም ብሉ’ እያለ ለሕዝቡ ተናግሮአል።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እርሱ፦ ምር​ኮው የረ​ዘመ ነውና ቤት ሠር​ታ​ችሁ ተቀ​መጡ፤ አታ​ክ​ል​ትም ተክ​ላ​ችሁ ፍሬ​ዋን ብሉ ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢ​ሎን ልኮ​አ​ልና።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እርሱ፦ ምርኮው የረዘመው ነውና ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፥ አታክልትንም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢሎን ልኮአልና።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 29:28
3 Cross References  

ቤቶችን ሠርታችሁ ተቀመጡ፤ አታክልትም ትከሉ፤ ፍሬዋንም ብሉ፤


“ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህችም ስፍራ እናንተን በመመለስ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።


ነቢዩ ኤርምያስ ተማርከው ወደ ተረፉት ሽማግሌዎች፥ ወደ ካህናቱም፥ ወደ ነቢያቱም፥ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃላት ይህ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements