Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 29:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህኑም ወደ መዕሤያ ልጅ ወደ ሶፎንያስ፥ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በስምህ እንዲህ ስትል ልከሃል፦

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በኢየሩሳሌም ላለው ሕዝብ ሁሉ፣ ለካህኑ ለመዕሤያ ልጅ ለሶፎንያስና ለሌሎችም ካህናት ሁሉ በገዛ ስምህ ደብዳቤዎችን ልከሃል፤ ለሶፎንያስም እንዲህ ብለሃል፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህ​ኑም ወደ ማሴው ልጅ ወደ ሶፎ​ን​ያስ፥ ወደ ካህ​ና​ቱም ሁሉ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን በስሜ እን​ዲህ ስትል ልከ​ሃል፦

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህኑም ወደ መዕሤያ ልጅ ወደ ሶፎንያስ፥ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በስምህ እንዲህ ስትል ልከሃል፦

See the chapter Copy




ኤርምያስ 29:25
16 Cross References  

የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን በማዕረጉም ሁለተኛ የነበረውን ካህን ሶፎንያስን የደጃፉም ጠባቂዎች የነበሩትን ሦስቱን ሰዎች ወሰደ፤


ንጉሡም ሴዴቅያስ፦ “እባክህ፥ ወደ አምላካችን ወደ ጌታ ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ።


ካህኑም ሶፎንያስ ይህን ደብዳቤ በነቢዩ በኤርምያስ ጆሮ አነበበው።


በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ።


በተጨማሪም መልካም ሥራውን በፊቴ ይናገሩ ነበር፥ እኔ ያልሁትንም ለእርሱ ይነግሩት ነበር፤ ጦቢያም ሊያስፈራራኝ ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር።


ደግሞም በእነዚያ ቀኖች የይሁዳ መኳንንቶች ብዙ ደብዳቤዎቻቸውን ወደ ጦቢያ ይልኩ ነበር፥ የጦብያም ወደ እነርሱ ይመጡ ነበር።


ከዚህም በኋላ ሰንባላጥ የተከፈተ ደብዳቤ በእጁ አስይዞ ይህንኑ ቃል በአገልጋዩ ለአምስተኛ ጊዜ ላከብኝ፤


ደግሞም የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመስደብ፥ በእርሱም ላይ ለመናገር፦ “የምድር አሕዛብ አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ ለማዳን እንዳልቻሉ፥ እንዲሁ የሕዝቅያስ አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊያድን አይችልም” የሚል ደብዳቤ ጻፈ።


ንጉሥ ሕዝቅያስ ደብዳቤውን ከመልክተኞች ተቀብሎ አነበበው፤ ወደ ቤተ መቅደስም ወስዶ ደብዳቤውን በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው፤


በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፦


ነቢዩ ኤርምያስ ተማርከው ወደ ተረፉት ሽማግሌዎች፥ ወደ ካህናቱም፥ ወደ ነቢያቱም፥ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃላት ይህ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements