ኤርምያስ 28:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፥ ከምድር ላይ አስወግድሃለሁ፤ በጌታ ላይ ዓመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ’ ” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ፤ በእግዚአብሔርም ላይ ዐመፅ ተናግረሃልና፣ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።’ ” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ስለዚህም እግዚአብሔር ‘አንተን ከምድረ ገጽ አስወግድሃለሁ ይህ ሕዝብ በእኔ በአምላካቸው ላይ እንዲያምፁ በማድረግህ ምክንያት ይህ ዓመት ከመፈጸሙ በፊት ትሞታለህ’ ይላል።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስወግድሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ዐመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከምድር ላይ እሰድድሃለሁ፥ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ አለው። See the chapter |