Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 28:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እንዲያገለግሉት የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ፤ እነርሱም ያገለግሉታል፥ ሌላው ቀርቶ የምድረ በዳ አራዊትን ሰጥቼዋለሁ።’ ”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እንዲያገለግሉ፣ በእነዚህ ሕዝቦች ላይ የብረት ቀንበር አደርጋለሁ፤ እነርሱም ይገዙለታል፤ በዱር አራዊት ላይ እንኳ ሥልጣን እሰጠዋለሁ።’ ”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በእነዚህ ሕዝቦች ሁሉ ጫንቃ ላይ የብረት ቀንበር እጭናለሁ፤ እነርሱም ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ይገዙለታል፤ ሌላው ቀርቶ የምድረ በዳ እንስሶች ሁሉ እንዲገዙለት አደርጋለሁ፤’ እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ይገ​ዙ​ለት ዘንድ የብ​ረ​ትን ቀን​በር በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ አን​ገት ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይገ​ዙ​ለ​ታል፤ የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትን ደግሞ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ይገዙለት ዘንድ የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ፥ እነርሱም ይገዙለታል፥ የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 28:14
13 Cross References  

ጌታ የሚያስነሣብህን ጠላቶችህን ታገለግላለህ፤ በራብና በጥማት፥ በእርዛትና በማጣት እስኪያጠፉህም ድረስ በዐንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭኑብሃል።


አሁን ደግሞ፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በበጎ ዐይን እመለከትሀለው፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ቅር፤ እነሆ ተመልከት፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ለመሄድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ትክክልም ነው ብለህ ወደምታስበው ስፍራ ወደዚያ ሂድ።


ለጌቶቻቸውም እንዲነግሩ እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ለጌቶቻችሁ እንዲህ በሉ፦


እናንተን ግን ጌታ ወስዶ፥ እንደ ዛሬው ሁሉ የርስቱ ሕዝብ እንድትሆኑለት፥ ከብረት እቶን ከግብጽ አውጥቷችኋል።


በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን?


ነገር ግን ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማያገለግለውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ያን ሕዝብ እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ።


ኖን። የኃጢአቶቼ ቀንበር በእጁ ተይዛለች፥ ታስረው በአንገቴ ላይ ወጥተዋል፥ ጉልበቴን አደከመ። ጌታ በፊታቸው እቆም ዘንድ በማልችላቸው እጅ አሳልፎ ሰጠኝ።


ኤፍሬም ማበራየት የምትወድ የተገራች ጊደር ነበር፥ እኔም በውብ አንገትዋ ላይ አልጫንኩባትም፤ በኤፍሬም ላይ እጠምድበታለሁ፥ ይሁዳም ያርሳል፥ ያዕቆብም ለራሱ አፈሩን ያለሰልሳል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements