ኤርምያስ 27:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 እነርሱ ግን ነቢያት ቢሆኑ፥ የጌታም ቃል በእነርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በጌታ ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይሄዱ እስቲ ወደ ሠራዊት ጌታ ይማለሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 እውነተኞች ነቢያት ከሆኑና በርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ካላቸው፣ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይወሰዱ ወደ ሰራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር እስኪ ይማልዱ! See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 እነርሱ ነቢያት ከሆኑና እኔም የሰጠኋቸው የትንቢት ቃል በእነርሱ ዘንድ ካለ፥ ገና ያልተወሰደው በቤተ መቅደስ፥ በይሁዳ ቤተ መንግሥትና በኢየሩሳሌም የቀረው ዕቃ ሁሉ ወደ ባቢሎን እንዳይወሰድ አደርግ ዘንድ እየተማጠኑ ሁሉን ቻይ የሆንኩትን እኔን እግዚአብሔርን ይጠይቁኝ።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 እነርሱ ግን ነቢያት ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በእነርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይሄዱ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር ይማለሉ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እነርሱ ግን ነቢያት ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በእነርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም የቀረችው ዕቃ ወደ ባቢሎን እንዳትሄድ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር ይማለሉ። See the chapter |