Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 22:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ብዙ አሕዛብም በዚህች ከተማ አጠገብ ያልፋሉ፥ ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፦ ጌታ በዚህች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደርገ?” ይላሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ከተለያየ አገር የመጡ ሕዝቦች በዚህች ከተማ በኩል ሲያልፉ፣ ‘እግዚአብሔር በዚህች ታላቅ ከተማ ላይ ለምን እንዲህ አደረገ?’ እያሉ እርስ በርስ ይነጋገራሉ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “ከዚያን በኋላ በዚያ በኩል የሚያልፉ ብዙ የውጪ አገር ሰዎች ‘በዚህች በታላቅ ከተማ ላይ እግዚአብሔር ይህን ጥፋት ያመጣው ለምን ይሆን?’ በማለት እርስ በርሳቸው ይጠያየቃሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ብዙ አሕ​ዛ​ብም በዚች ከተማ ላይ ያል​ፋሉ፤ ሁሉም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚች ታላቅ ከተማ ለምን እን​ዲህ አደ​ረገ? ይላሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ብዙ አሕዛብም በዚህች ከተማ አጠገብ ያልፋሉ፥ ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፦ እግዚአብሔር በዚህች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደርገ? ይላሉ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 22:8
13 Cross References  

ላሜድ። የምድር ነገሥታት በዓለምም የሚኖሩ ሁሉ አስጨናቂና ጠላት በኢየሩሳሌም በር እንዲገባ አላመኑም።


“ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃላት ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ‘ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገርን ለምን ጌታ ተናገረብን? በደላችንስ ምንድነው? በአምላካችንስ በጌታ ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድነው?’ ቢሉህ፥


የዘበኞቹም አለቃ ኤርምያስን ወሰደው እንዲህም አለው፦ “ጌታ አምላክህ ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተናገረ፤


በአንቺ ላይ በንዴትና በቁጣ፥ በመዓትም ዘለፋ ፍርድን ባደረግሁብሽ ጊዜ፥ በዙሪያሽ ላሉ አገሮች መሰደቢያና መተረቻ፥ ማስጠንቀቂያና ድንጋጤ ትሆኛለሽ፥ እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።


በሚሄዱባቸው አሕዛብ መካከል ርኩሰታቸውን ሁሉ እንዲናገሩ ከእነርሱ ጥቂቶች ከሰይፍ፥ ከራብና ከቸነፈር አስቀራለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


መንገዳቸውንና ሥራቸውን ባያችሁ ጊዜ ያጽናኑአችኋል፥ ያደረግሁትም ሁሉ በከንቱ እንዳላደረግሁት ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የእስራኤል ቤት በበደላቸው ምክንያት እንደ ተማረኩ አሕዛብ ያውቃሉ፤ እኔን ስለ በደሉኝ፥ እኔም ፊቴን ከእነርሱ ሰወርሁ፥ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ ሁሉም በሰይፍ ወደቁ።


ጌታም አመጣው፥ እንደ ተናገረውም አደረገ፤ በጌታም ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና፥ ድምፁንም አልሰማችሁምና ይህ ነገር በእናንተ ላይ ሆነ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements