ኤርምያስ 22:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 እረኞችሽን ሁሉ ንፋስ ያሰማራቸዋል፥ ውሽሞችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ በዚያን ጊዜም ስለ ኃጢአትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ ትዋረጃለሽም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 እረኞችሽ ሁሉ በነፋስ ይወሰዳሉ፤ ወዳጆችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ ከክፋትሽም ሁሉ የተነሣ፣ ታፍሪያለሽ፤ ትዋረጂያለሽም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 በምትሠሩት ኃጢአት ምክንያት ነፋስ ገለባን ጠራርጎ እንደሚወስድ፥ መሪዎቻችሁ ተጠራርገው ይወሰዳሉ። የተማመናችሁባቸው የጦር ጓደኞቻችሁም ተማርከው ወደ ባዕድ ሀገር ይወሰዳሉ፤ ኀፍረትና ውርደትም ይደርስባችኋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይወስዳቸዋል፤ ወዳጆችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ፤ በወዳጆችሽም ፊት ቷረጃለሽ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥ ውሽሞችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፥ በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ ትጐሳቈይማለሽ። See the chapter |