ኤርምያስ 21:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በጫካዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፥ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እንደ ሥራችሁ መጠን እቀጣችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በዱሯም እሳት እለኵሳለሁ፤ በዙሪያዋ ያለውንም ሁሉ ይበላል።’ ” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ነገር ግን ስላደረግሽው ነገር ሁሉ እኔ እቀጣሻለሁ፤ ቤተ መንግሥትሽ በእሳት እንዲቃጠል አደርጋለሁ፤ ያም እሳት በዙሪያው የሚገኘውን ነገር ሁሉ ያጋያል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፥ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል። See the chapter |