ኤርምያስ 20:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አንተም፥ ጳስኮር ሆይ! በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ፤ አንተም በሐሰት ትንቢት የተናገርህላቸው ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎን ትገባላችሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ፥ በዚያም ትቀበራላችሁ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ጳስኮር ሆይ፤ አንተና በቤትህ የሚኖሩት ሁሉ ወደ ባቢሎን ትጋዛላችሁ። አንተና በሐሰት ትንቢት የተነበይህላቸው ወዳጆችህ በዚያ ትሞታላችሁ፤ በዚያም ትቀበራላችሁ።’ ” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ፓሽሑር ሆይ! አንተም ራስህና ቤተሰብህ በሙሉ ተማርካችሁ ወደ ባቢሎን ትወሰዳላችሁ፤ በሐሰት ከተነበይክላቸው ከወዳጆችህ ሁሉ ጋር ሞተህ በዚያው ትቀበራለህ።’ ” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 አንተም ጳስኮር ሆይ! በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ፤ አንተም በሐሰት ትንቢት የተናገርህላቸው ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎን ትገባላችሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ፤ በዚያም ትቀበራላችሁ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 አንተም፥ ጳስኮር ሆይ፥ በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ፥ አንተም በሐሰትም ትንቢት የተናገርህላቸው ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎን ትገባላችሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ፥ በዚያም ትቀበራላችሁ። See the chapter |