ኤርምያስ 20:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ጌታ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘለዓለምም በማይረሳ ውርደት ይዋረዳሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋራ ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እግዚአብሔር ግን እንደ ጀግና ወታደር ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ በመደናቀፍ ኀይል አጥተው ይወድቃሉ። በሚወድቁበትም ጊዜ ክፉኛ ይዋረዳሉ፤ ውርደታቸውም ለረጅም ጊዜ ይታወሳል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እግዚአብሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆች ይሰናከላሉ፤ አያሸንፉም፤ ለዘለዓለምም የማይረሳ ጕስቍልናቸውን አላወቁምና ፈጽመው አፈሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው፥ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፥ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጐሰቍላሉ። See the chapter |