Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 18:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “የእስራኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አልችልምን? ይላል ጌታ፤ እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ የእስራኤል ቤት ሆይ! እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ አላችሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ሸክላ ሠሪው እንደሚሠራው፣ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አይቻለኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ጭቃው በሸክላ ሠሪው እጅ እንዳለ፣ እናንተም እንዲሁ በእጄ ውስጥ ናችሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ሸክላ ሠሪው ሸክላውን በፈለገው ዐይነት እንደሚሠራው፥ እኔስ በእናንተ ላይ የፈለግኹትን ማድረግ አልችልምን? የሸክላው ጭቃ በሸክላ ሠሪው እጅ እንደሚገኝ እናንተም፥ በእኔ እጅ ናችሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እን​ደ​ሚ​ሠራ በውኑ እኔ በእ​ና​ንተ ዘንድ መሥ​ራት አይ​ቻ​ለ​ኝ​ምን? እነሆ ጭቃው በሸ​ክላ ሠሪ እጅ እን​ዳለ፥ እን​ዲሁ እና​ንተ በእኔ እጅ አላ​ችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምን? እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ እንዲሁ እናንተ በእኔ እንጅ አላችሁ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 18:6
8 Cross References  

አሁን ግን፥ አቤቱ ጌታ፥ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።


ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?


ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፥ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።


የራሴ በሆነ ነገር ላይ የወደድሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንኩ ትመቀኛለህን?


“የጌታን ልብ የሚያውቅ ማን ነው?” “ወይስ አማካሪው የሆነ ማን ነው?


የጌታም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements