ኤርምያስ 17:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 የሚቃጠለው መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትን፥ የእህሉንም ቁርባን ዕጣኑንም፥ የምስጋናውንም መሥዋዕት ይዘው ከይሁዳ ከተሞች ከኢየሩሳሌምም ዙሪያ፥ ከብንያምም አገር፥ ከቈላውም ከደጋውም ከደቡብም ወደ ጌታ ቤት ይመጣሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ሰዎች ከይሁዳ ከተሞች፣ ከኢየሩሳሌም ዙሪያ፣ ከብንያምም አገር፣ ከቈላውና ከደጋው አገር እንዲሁም ከኔጌብ የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ ዕጣንና የምስጋና መሥዋዕት ይዘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ከይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከሚገኙ መንደሮች ሕዝቡ በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ ከብንያም ክፍል፥ ከኰረብቶች ግርጌ፥ ከተራሮችና ከይሁዳ ደቡብ ይመጣሉ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላውንም መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባንና ዕጣን፥ የምስጋናውንም መሥዋዕት ጭምር ወደ ቤተ መቅደሴ ያመጣሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉንም ቍርባን፥ እጅ መንሻውንና ዕጣኑን፥ የምስጋናውንም መሥዋዕት ይዘው ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ዙሪያ፥ ከብንያምም ሀገር፥ ከቆላውም፥ ከደጋውም፥ ከደቡብም ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 የሚቃጠለው መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትን የእህሉንም ቍርባን ዕጣኑንም የምስጋናውንም መሥዋዕት ይዘው ከይሁዳ ከተሞች ከኢየሩሳሌምም ዙሪያ ከብንያምም አገር ከቈላውም ከደጋውም ከደቡብም ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ። See the chapter |