ኤርምያስ 17:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ከቤቶቻችሁም በሰንበት ቀን ሸክምን አታውጡ፥ ሥራንም ሁሉ አትሥሩበት፤ አባቶቻችሁንም እንዳዘዝሁ የሰንበትን ቀን ቀድሱ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 አባቶቻችሁን እንዳዘዝኋቸው ሰንበትን አክብሩ እንጂ በሰንበት ቀን ከየቤታችሁ ሸክም ይዛችሁ አትውጡ፤ ምንም ሥራ አትሥሩ።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 የቀድሞ አባቶቻችሁን እንዳዘዝኳቸው ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርጋችሁ አክብሩ እንጂ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ ከቤታችሁ አትውጡ፤ በሰንበት ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ከቤቶቻችሁ በሰንበት ቀን ሸክምን አታውጡ፤ ሥራንም ሁሉ አትሥሩ፤ አባቶቻችሁንም እንዳዘዝኋቸው የሰንበትን ቀን ቀድሱ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ከቤቶቻችሁም በሰንበት ቀን ሸክምን አታውጡ፥ ሥራንም ሁሉ አትሥሩበት፥ አባቶቻችሁንም እንዳዘዝሁ የሰንበትን ቀን ቀድሱ። See the chapter |