Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኤርምያስ 10:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፥ በምድሪቱ የሚኖሩትን እስኪሰማቸው ድረስ በዚህ ጊዜ እወነጭፋቸዋለሁ፥ አስጨንቃቸዋለሁም።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “በዚህች ምድር የሚኖሩትን፣ አሁን ወደ ውጪ እወነጭፋቸዋለሁ፤ ጕዳቱ እንዲሰማቸው፣ መከራ አመጣባቸዋለሁ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚህ ጊዜ በዚህች አገር የሚኖሩትን ሰዎች አስወጣለሁ፤ እነርሱን አስጨንቄ እንዲማረኩ አደርጋለሁ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ በም​ድ​ሪቱ የሚ​ኖ​ሩ​ትን በመ​ከራ አሰ​ና​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ሽም እን​ዲ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ በምድሪቱ የሚኖሩትን እስኪሰማቸው ድረስ በዚህ ጊዜ እወነጭፋቸዋለሁ፥ አስጨንቃቸውማለሁ።

See the chapter Copy




ኤርምያስ 10:18
11 Cross References  

ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፥ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በጌታ ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፥ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል።


ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።


እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ፥ ይህን ክፉ ነገር እንደማመጣባቸው መናገሬ በከንቱ አይደለም።


የጌታ ቁጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም፤ በኋለኛው ዘመን ፈጽማችሁ ታስተውሉታላችሁ።


ስለዚህ ከዚህች ምድር እናንተና አባቶቻችሁ ወዳላወቃችኋት ምድር እጥላችኋለሁ፤ ምሕረትንም አላደርግላችሁምና በዚያ ሌሎችን አማልክት ቀንና ሌሊት ታገለግላላችሁ።’


የምትተማመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪማረኩ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከባል፤ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወራቸዋል።


አንተንም የወለደችህንም እናትህን ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ አገር እጥላችኋለሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ።


በሰዎች ላይ ጭንቀትን አመጣለሁ፤ እንደ ዕውርም ይሄዳሉ፥ በጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርተዋልና፤ ደማቸው እንደ ትቢያ ይፈስሳል፥ ሥጋቸውም እንደ ጉድፍ ይጣላል።


እነሆ ወዳጄ፥ ጌታ በኃይል ወርውሮ ይጥልሃል፥ አጥብቆም ሊጨብጥህ ነው፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements