ያዕቆብ 4:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 እናንተ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ወይም ወደዚያች ከተማ እንሄዳለን፤ በእርሷም አንድ ዓመት እንቈያለን፤ እንነግዳለን፤ እናተርፋለንም” የምትሉ ተመልከቱ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 እናንተ፣ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ወይም ወደዚያች ከተማ እንሄዳለን፤ በርሷም አንድ ዓመት እንቈያለን፤ እንነግዳለን፤ እናተርፋለንም” የምትሉ እንግዲህ ስሙ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እናንተ “ዛሬ ወይም ነገ ወደ እንዲህ ያለ ከተማ ሄደን እዚያ አንድ ዓመት እንቀመጣለን፤ ነግደንም እናተርፋለን” የምትሉ ተጠንቀቁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 አሁንም “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን፤ በዚያም ዓመት እንኖራለን፤ እንነግድማለን፤ እናተርፍማለን፤” የምትሉ እናንተ! ተመልከቱ፤ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 አሁንም፦ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። See the chapter |