ኢሳይያስ 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፤ ድንቅ መካር፤ ኀያል አምላክ፤ የዘለዓለም አባት፤ የሰላም ልዑል ይባላል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣ ለእሳት ይዳረጋል፤ ይማገዳልም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የወራሪ ጦረኞች ጫማና በደም የተለወሰ ልብሳቸው ሁሉ በእሳት ይጋያል። እንደ ማገዶ ሆኖ ይቃጠላል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 በደም የተለወሰ ልብስ በእሳት ከሚቃጠል በቀር ለምንም አይጠቅምም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የሚረግጡ የሠልፈኞች ጫማ ሁሉ፥ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፥ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል። See the chapter |