Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 9:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሽማግሌዎችና የተከበሩ ሰዎች ራስ፤ ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ደግሞ ጅራት ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ እግዚአብሔር ራስንና ጅራትን፣ የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸንበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ እግዚአብሔር በአንድ ቀን እንደ ራስና እንደ ጅራት እንደ ዘንባባውና እንደ ቅርንጫፉ የሚቈጠሩትን ከእስራኤል ይቈርጣል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራስ​ንና ጅራ​ትን፥ ታላ​ቁ​ንና ታና​ሹን በአ​ንድ ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤል ይቈ​ር​ጣል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ስለዚህ እግዚአብሔር እራስንና ጅራትን፥ የሰሌኑን ቅርንጫፍና እንግጫውን በአንድ ቀን ከእስራኤል ይቆርጣል።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 9:14
28 Cross References  

ስለዚህም ሞትና ኀዘን፥ ራብም የሆኑት መቅሰፍቶችዋ በአንድ ቀን ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”


ራስ ይሁን ጅራት፥ የዘንባባ ዝንጣፊ ይሁን ደንገል፥ ለግብጽ አንዳች ነገር ሊያደርጉላት አይችሉም።


ይህን የሚያህል ታላቅ ሀብት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና፤” የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፤


ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ውስጥ ፍርድሽ ይፈጸማልና፤” እያሉ ይናገራሉ።


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ምድርህም በገመድ እየተለካች ትከፋፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፥ እስራኤልም ያለ ጥርጥር ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።’ ”


እነሆም፥ ጌታ ያዝዛል፤ ታላቁንም ቤት በማፍረስ፥ ታናሹንም ቤት በመሰባበር ይመታል።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግርን ወይም የጆሮን ጫፍ እንደሚያድን፥ እንዲሁ በሰማርያ የተቀመጡት የእስራኤል ልጆች ከድንክ አልጋና ከአልጋ የእግር ቁራጭ ጋር ይድናሉ።”


ስለዚህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥዋትም እንደሚያልፍ ጠል፥ በዐውሎ ነፍስም ከአውድማ እንደሚበተን እብቅ፥ ከመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።


ቤቴል ሆይ! ከኃጢአታችሁም ክፋት የተነሣ እንዲሁ ይደረግባችኋል፤ ጎሕ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።


እስራኤል ተውጦአል፤ አሁን በአሕዛብ መካከል እንደ ረከሰ ዕቃ ሆነዋል።


በቀንም ትሰናከላለህ፥ እንዲሁም ነቢይ ከአንተ ጋር በሌሊት ይሰናከላል፤ እናትህንም አጠፋታለሁ።


ጌታም፦ “ሕዝቤ አይደላችሁምና፥ እኔም አምላካችሁ አይደለሁምና ስሙን ሎዓሚ ብለህ ጥራው፥” አለው።


ዳግመኛም ፀነሰች ሴት ልጅም ወለደች። ጌታም እንዲህ አለው፦ “የእስራኤልን ቤት ፈጽሞ ይቅር እንድላቸው ከእንግዲህ ወዲህ ርኅራኄ የለኝምና ስምዋን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት፤


ጌታም እንዲህ አለው፦ “ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በኢዩ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፤


ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።


የእስራኤል ብርሃን እሳት፤ ቅዱሱም ነበልባል ይሆናል፤ በአንድ ቀንም እሾኹንና ኩርንችቱን እሳት ይበላዋል፤


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፥ ከዚህ ሕዝብ ፊት ዕንቅፋቶችን አደርጋለሁ፤ አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል፥ ጎረቤትና ባልንጀራውም ይጠፋሉ።’ ”


አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል ጌታ።”


ዔ። የእግዚአብሔር ፊት በተናቸው እርሱም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፥ የካህናቱን ፊት አላፈሩም፥ ሽማግሌዎቹንም አላከበሩም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements