ኢሳይያስ 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ነገር ግን ጌታ የረአሶንን ጠላቶች ያጠናክራል፤ በእነርሱም ላይ ያመጣባቸዋል፤ ባለጋራዎቻቸውንም ያነሣሣባቸዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 “ጡቦቹ ወድቀዋል፤ እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤ የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤ እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 “ከጡብ የተሠሩ ግንቦች ፈርሰዋል፤ እኛ ግን እንደገና በጥርብ ድንጋይ እንገነባቸዋለን፤ ከሾላ ግንድ የተሠሩ ምሰሶዎች ተሰብረዋል፤ እኛ ግን በምርጥ የሊባኖስ ዛፍ እንተካቸዋለን።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 “ጡቡ ወደቀ፤ ነገር ግን ኑ፥ ድንጋይ እንውቀር፤ ሾላው ነቀዘ፤ ነገር ግን ፅድን እንቍረጥ፤ ለራሳችንም ግንብን እንሥራ።” See the chapter |