Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 8:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ተጨንቀውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ክፉኛ ሲራቡም ይቈጣሉ፤ ወደ ላይ እየተመለከቱ ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይራገማሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ተጨንቀውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ክፉኛ ሲራቡም ይቈጣሉ፤ ወደ ላይ እየተመለከቱ ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይራገማሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሕዝቡ ተስፋ ቈርጠውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ከመራባቸው የተነሣ ተበሳጭተው ወደ ሰማይ እያንጋጠጡ ንጉሣቸውንና አማልክታቸውን ይራገማሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በዚ​ህም በር​ግጥ ጽኑ ረኃብ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋል፤ በተ​ራ​ባ​ች​ሁም ጊዜ ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ፤ በአ​ለ​ቆ​ችና በመ​ኳ​ን​ን​ቱም ላይ ክፉ ትና​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ወደ ላይ ወደ ሰማይ ትመ​ለ​ከ​ታ​ላ​ችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እነርሱም ተጨንቀውና ተርበው ያልፋሉ፥ በተራቡም ጊዜ ተቈጥተው ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይረግማሉ፥ ወደ ላይም ይመለከታሉ፥

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 8:21
25 Cross References  

ምናሴ ኤፍሬምን፤ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።


የሰው ስንፍና መንገዱን ታጣምምበታለች፥ ልቡም በጌታ ላይ ይቈጣል።


በአራተኛውም ወር በዘጠነኛው ቀን በከተማይቱ ራብ ጸንቶ ነበር፥ ለአገሬውም ሰው እንጀራ ታጣ።


ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ ደዌ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቁት አገር ሄደዋልና።’”


ሚስቱም፦ “እስከ አሁን ፍጹምነትህን ይዘሃልን? እግዚአብሔርን ስደብና ሙት” አለችው።


ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሥጋውን ዳስስ፥ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል።”


ነገር ግን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ዳስስ፥ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል።”


በዚያው ዓመት አራተኛው ወር በገባ በዘጠነኛው ቀን ራቡ በጣም ስለ ጸና ሕዝቡ የሚመገበው አንዳችም ምግብ አልነበረም።


ከሙላትህና ከጭማቂህ ለማቅረብ አትዘግይ፤ የልጆችህንም በኩር ትሰጠኛለህ።


ገና ይህን ተናግሮ ሳይጨርስ ንጉሡ ድንገት ከተፍ ብሎ “ይህን መከራ በእኛ ላይ ያመጣብን እግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ እርሱ አንድ ነገር ያደርግ ዘንድ ከዚህ በላይ ምን ልጠብቅ?” አለ።


የእስራኤላዊቱም ልጅ የጌታን ስም ሰደበ፥ አቃለለውም፤ ወደ ሙሴም አመጡት። እናቱም ከዳን ነገድ የደብራይ ልጅ ነበረች፥ ስምዋም ሰሎሚት ነበረ።


ያም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ከመረጣችሁት ንጉሥ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ ነገር ግን በዚያ ቀን ጌታ አይመልስላችሁም።”


ኃይሉ በራብ ትደክማለች፥ መቅሠፍትም እስኪሰናከል ተዘጋጅቶለታል።


የድሆችም የበኩር ልጆች ይሰማራሉ፥ ችግረኞችም ተዘልለው ይተኛሉ፤ ሥርህንም በራብ እገድላለሁ፥ ቅሬታህም ይገደላል።


እነዚህ ሁለት ነገሮች ሆነውብሻል፥ ማንስ ያስተዛዝንሻል? መፈታትና ጥፋት፥ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እንዴትስ አድርጌ አጽናናሻለሁ?


ስለዚህ ፍርድ ከእኛ ዘንድ ርቆአል፥ ጽድቅም አላገኘንም፤ ብርሃንን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፥ እነሆም፥ ጨለማ ሆነ፤ ጸዳልን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፥ ነገር ግን በጨለማ ሄድን።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ይበላሉ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ደስ ይላቸዋል እናንተ ግን ታፍራላችሁ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements