ኢሳይያስ 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፤ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የሚያመጣውም የአሦርን ንጉሥ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፣ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የሚያመጣውም የአሦርን ንጉሥ ነው።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 “እነሆ እግዚአብሔር እስራኤል ከይሁዳ ከተለየበት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቀውን የመከራ ዘመን በአንተና በሕዝብህ፥ በአባትህም ንጉሣዊ ቤተሰብ ላይ ያመጣል፤ ይኸውም የአሦርን ንጉሥ ያመጣብሃል ማለት ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፥ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው። See the chapter |