ኢሳይያስ 66:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በመሀከላቸው ያለውን አንዱን ተከትለው ወደ መናፈሻ ስፍራው ለመግባት ሰውነታቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፥ የእሪያንም ሥጋ፥ አስጸያፊ ነገርንም፥ አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፥ ይላል ጌታ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “ወደ አትክልት ቦታዎች ለመሄድና ከተክሎቹ አንዱን ለማምለክ ራሳቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፣ የዕሪያዎችንና የዐይጦችን ሥጋ፣ የረከሱ ነገሮችንም የሚበሉ ሁሉ የመጨረሻ ፍርዳቸውን በአንድነት ይቀበላሉ” ይላል እግዚአብሔር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእርያ ሥጋና አይጥ፥ እንዲሁም ሌሎች አጸያፊ ነገሮች ከሚበሉት ሰዎች መካከል አንዱን ተከትለው ወደ አትክልቶቹ ቦታዎች ለመሄድ ራሳቸውን የሚለዩና የሚያነጹ በአንድነት ይጠፋሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 “በአትክልት ቦታ ውስጥ ሰውነታቸውን የሚያጠሩና የሚያነጹ፥ በምግብ ቦታም የእሪያን ሥጋ፥ አስጸያፊ ነገርንም አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በመካከላቸው ያለውን እንዱን ተከትለው ወደ ገነቱ ይገቡ ዘንድ ሰውነታቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፥ የእሪያንም ሥጋ አስጸያፊ ነገርንም አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። See the chapter |