ኢሳይያስ 65:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ተኩላና ጠቦት በአንድነት ይሠማራሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ጉዳት አያደርሱም፥ አያጠፉምም፥ ይላል ጌታ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ተኵላና የበግ ጠቦት በአንድነት ይበላሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ እባብ ትቢያ ይልሳል፤ በተቀደሰው ተራራዬም፣ ጕዳት አያደርሱም፤ ጥፋት አያመጡም፤” ይላል እግዚአብሔር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ተኲላና ጠቦት አብረው ይመገባሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብ ምግብ ትቢያ ይሆናል፤ እነርሱም በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፤ አያጠፉምም” ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ያንጊዜ ተኵላና በግ በአንድነት ይሰማራሉ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፤ አያጠፉምም፥” ይላል እግዚአብሔር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ተኵላና ጠቦት በአንድነት ይሠማራሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፥ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፥ አያጠፉምም፥ ይላል እግዚአብሔር። See the chapter |