ኢሳይያስ 65:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ላልጠየቁኝ ተገለጥሁ፥ ላልፈለጉኝም ተገኘሁ፤ በስሜም ያልተጠራውን ሕዝብ፦ “አለሁኝ፥ አለሁኝ” አልኩት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 “ላልጠየቁኝ ራሴን ገለጥሁላቸው፤ ላልፈለጉኝ ተገኘሁላቸው። ስሜን ላልጠራ ሕዝብ፣ ‘አለሁልህ፤ አለሁልህ’ አልሁት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ላልጠየቁኝ ተገለጥኩላቸው፤ ላልፈለጉኝም ተገኘሁላቸው፤ ስሜንም ላልጠራ ሕዝብ ‘እነሆ፥ እዚህ አለሁ፥ እነሆ፥ እዚህ አለሁ’ አልኳቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ያልፈለጉኝ አገኙኝ፤ ላልጠየቁኝም ተገኘሁ፤ ስሜን ላልጠራ ሕዝብ፥ “እነሆኝ” አልሁት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ላልጠየቁኝ ተገለጥሁ፥ ላልፈለጉኝም ተገኘሁ፥ በስሜም ያልተጠራውን ሕዝብ፦ እነሆኝ፥ እነሆኝ አልሁት። See the chapter |