ኢሳይያስ 64:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ማንም አልሰሙም፥ የትኛውም ጆሮ አልተቀበለውም፥ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላችው ከአንተ አምላካችን በቀር ሌላ ማንም አላየውም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ከጥንት ጀምሮ፣ በተስፋ ለሚጠባበቁት የሚደርስላቸው፣ ከአንተ በቀር አምላክ እንዳለ ያየ ዐይን የለም፤ የሰማም ጆሮ የለም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ከጥንት ጀምሮ ተስፋቸውን በእርሱ አድርገው ለሚተማመኑበት ወገኖች እነዚያን ሁሉ ድንቅ ነገሮች ያደረገ አምላክ ከአንተ በቀር አልተሰማም፤ አልታየም፤ የተረዳም የለም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ከጥንት ጀምሮ ይቅርታህን ለሚጠባበቁ ምሕረትን ከምታደርግላቸው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ አላየንም፤ አልሰማንምም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላችው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክን አልሰሙም በጆሮአቸውም አልተቀበሉም ዓይንም አላየችም። See the chapter |