ኢሳይያስ 64:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ እንዲገለጥ፥ አሕዛብም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ ውሃንም እንደሚያፈላ፣ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤ መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ! See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እሳት ደረቁን እንጨት በሚያጋይ ጊዜ ፍሙ የተጣደውን ውሃ እንደሚያፍለቀልቀው፥ ሕዝቦችም በአንተ መገለጥ እንዲንቀጠቀጡ ወርደህ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ አድርግ! See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 አደሮ ማር በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ እንዲሁ ጠላቶችህን እሳት ትበላቸዋለች፤ ስምህም በእነርሱ ላይ ይታወቃል፤ አሕዛብም በፊትህ ይደነግጣሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፥ አህዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ። See the chapter |