ኢሳይያስ 63:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 በጭንቃቸው ሁሉ ተጨነቀ፤ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በምሕረቱ ዋጃቸው፤ በቀደመው ዘመን ሁሉ አነሣቸው፤ ተሸከማቸውም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 በችግራቸው ጊዜ ሁሉ ያዳናቸው በመልእክተኛ ወይም በመልአክ አማካይነት ሳይሆን እርሱ በመካከላቸው በመገኘት ነው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ታደጋቸው፤ እርሱም በቀድሞ ዘመናት ሁሉ አንሥቶ ልጁን እንደሚሸከም ሰው ተንከባከባቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በመልእክተኛም አይደለም፤ በመልአክም አይደለም፤ እርሱ ራሱ ያድናቸዋል እንጂ። እርሱ ይወዳቸዋልና፥ ይራራላቸዋልምና እርሱ ተቤዣቸው፤ ተቀበላቸውም፤ በዘመናቸውም ሁሉ ለዘለዓለም አከበራቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፥ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው። See the chapter |