ኢሳይያስ 63:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ተመለከትሁ፥ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፥ ቁጣዬም አጸናኝ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ተመለከትሁ፤ የሚረዳ ግን አልነበረም፤ የሚያግዝ ባለመኖሩም ተገረምሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ ድነትን አመጣልኝ፤ የገዛ ቍጣዬም አጸናኝ፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ዙሪያዬን በተመለከትኩ ጊዜ የሚረዳ ማንም አልነበረም። ደጋፊ ባለመኖሩ ተደነቅሁ፤ ስለዚህ በኀይለኛ ቊጣዬ አማካይነት እኔው ራሴ ድልን አመጣሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የሚረዳም እንደሌለ አየሁ፤ የሚያግዝም እንደሌለ ዐወቅሁ፤ ስለዚህ በገዛ ክንዴ አድናቸዋለሁ፤ ቍጣዬም ወደቀችባቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ተመለከትሁ፥ የሚረዳም አልተገኘም፥ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፥ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፥ ቍጣዬም እርሱ አገዘኝ። See the chapter |