Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 63:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “ቀሚስህ ስለምን ቀላ? ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለምን መሰለ?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 መጐናጸፊያህ፣ ለምን በወይን መጭመቂያ፣ ወይን እንደሚረግጡ ሰዎች ልብስ ቀላ?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የወይን ጠጅ ጨምቆ ለማውጣት የወይን ፍሬ ሲጨምቅ እንደ ነበረ ሰው ልብስህ ስለምን ቀይ ሆነ?”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ቀሚ​ስህ ስለ ምን ቀላ? ልብ​ስ​ህስ በወ​ይን መጭ​መ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ረ​ግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ቀሚስህ ስለ ምን ቀላ? ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ?

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 63:2
7 Cross References  

በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሏል።


አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።


መልአኩም ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፤ በምድርም ካለው ከወይን ዛፍ ቈርጦ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር የቁጣ ወይን መጥመቂያ ጣለ።


ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል፥ የአህያይቱንም ግልገል በወይን አረግ፥ ልብሱን በወይን ያጥባል፥ መጎናጸፊያውንም በወይን ደም።


ጽድቅንም እንደ ጥሩር ለበሰ፥ በራሱም ላይ የማዳንን ራስ ቁር አደረገ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፥ በቅንዓትም መጐናጸፊያ ተጐናጸፈ።


ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጉልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።”


ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ለደም አሳልፌ እሰጥሃለሁ ደምም ያሳድድሃል፥ ደምን ስላልጠላህ ደም ያሳድድሃል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements