ኢሳይያስ 60:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የመቅደሴንም ስፍራ ለማስጌጥ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው፥ ባርሰነቱም ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 “የመቅደሴን ቦታ ለማስጌጥ፣ የሊባኖስ ክብር፣ ጥዱ፣ አስታውና ባርሰነቱ በአንድነት ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ እግሬ የሚያርፍበትንም ስፍራ አከብራለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ቤተ መቅደሴ ያረፈበትን ቦታ ለማስዋብ የሊባኖስ ግርማ የሆኑት ዝግባ አስታና ጥድ ወደ አንቺ እንዲመጡ ይደረጋሉ፤ እኔም የእግሬ ማረፊያ የሆነውን አከብረዋለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የመቅደሴንም ስፍራ ያከብሩ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው፥ ባርሰነቱም ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የመቅደሴንም ስፍራ ያስጌጡ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው ባርሰነቱም፥ ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ። See the chapter |