ኢሳይያስ 59:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ፍትህም ወደ ኋላ ተመልሶአል፥ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፥ ቅንነትም ሊገባ አልቻለም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቋል፤ ጽድቅም በሩቁ ቆሟል፤ እውነት በመንገድ ላይ ተሰናክሏል፤ ቅንነትም መግባት አልቻለም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 በሕዝብ አደባባይ እውነት ስለ ተሰናከለና ታማኝነት ሊገባ ስላልቻለ ፍትሕ ወደ ኋላ ተመልሶአል፤ ጽድቅም ተዳክሞአል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ፍርድን ከመከተል ወደ ኋላ ርቀናል፤ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም ከመንገዳቸው ታጥቶአል፤ በቀና መንገድም መሄድ አልቻሉም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ፍርድም ወደ ኋላ ተመልሶአል፥ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፥ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፥ ቅንነትም ሊገባ አልቻለምና። See the chapter |