ኢሳይያስ 58:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነው? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነው? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ እንዲያደርግ፥ ማቅንና አመድንም በበታቹ እንዲያነጥፍ ነው? በውኑ ይህን ጾም፥ በጌታ ዘንድ የተወደደ ቀን ብለህ ትጠራዋለህ? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እኔ የመረጥሁት ጾም እንዲህ ዐይነቱን ነውን? ሰውስ ራሱን የሚያዋርደው በእንዲህ ያለው ቀን ብቻ ነውን? እንደ ደንገል ራስን ዝቅ ማድረግ ነውን? ወይስ ማቅ ለብሶ በዐመድ ላይ መንከባለል ነውን? ታዲያ ጾም ብለህ የምትጠራው ይህን ነውን? እግዚአብሔርስ የሚቀበለው እንዲህ ያለውን ቀን ነውን? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እናንተ በምትጾሙበት ጊዜ ሰውነታችሁን ታጐሳቊላላችሁ፤ ራሳችሁን እንደ ሸምበቆ ዝቅ ታደርጋላችሁ፤ አመድ ነስንሳችሁ፥ ማቅም አንጥፋችሁ ትተኛላችሁ? ታዲያ እናንተ ጾም የምትሉት ይህን ነውን? እኔስ በዚህ ዐይነቱ ጾም ደስ የሚለኝ ይመስላችኋልን? See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እኔ ይህን ጾም የመረጥሁ አይደለሁም፤ እንደዚችም ባለች ቀን ሰው ራሱን ቢያሳዝን፥ አንገቱንም እንደ ቀለበት ቢያቀጥን፥ ማቅ ለብሶ በአመድ ላይ ቢተኛም፥ ይህ ጾም በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠ አይደለም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለሁ? See the chapter |