ኢሳይያስ 54:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ይህ ለኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፤ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፥ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልዘልፍሽም ምያለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 “ይህ ለእኔ የኖኅ ውሃ ምድርን ዳግመኛ እንዳያጥለቀልቃት እንደማልሁበት፣ እንደ ኖኅ ዘመን ነው፤ አሁንም አንቺን ዳግም እንዳልቈጣ፣ እንዳልገሥጽሽም ምያለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 “በኖኅ ዘመን ‘ምድርን በውሃ መጥለቅለቅ እንደገና አላጠፋትም’ ብዬ ቃል እንደ ገባሁ እነሆ አሁንም ‘በአንቺ ላይ እንደገና አልቈጣም’ ብዬ ቃል እገባልሻለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ተግሣጽ አላደርስብሽም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ከኖኅ ዘመን ውኃ ጀምሮ ይህ ለእኔ ምስክር ነው፤ ቀድሞ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን እንዳልቈጣት እንደ ማልሁ፥ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ይህ ለኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፥ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፥ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልዘልፍሽም ምያለሁ። See the chapter |