ኢሳይያስ 53:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን እንደ ተመታ፥ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ፥ እንደ ስቃይተኛም ቈጠርነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣ እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 “በእውነት እርሱ ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር ተመትቶ እንደ ወደቀና እንደ ቈሰለ አድርገን ቈጠርነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እርሱ ግን በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ ስለ እኛም ታመመ፤ እኛም እንደ ታመመ፥ እንደ ተገረፈም ቈጠርነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፥ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። See the chapter |