ኢሳይያስ 51:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ሞገዱም እንዲተምም ባሕርን የማናውጥ አምላክህ ጌታ እኔ ነኝ፥ ስሜም የሠራዊት ጌታ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ሞገዱ እንዲተምም ባሕሩን የማናውጥ፣ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤ ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 “ማዕበሉ ይጮኽ ዘንድ ባሕሩን የማናውጥ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ባሕርን የማናውጥ፥ ሞገዱም እንዲተምም የማደርግ አማላክሽ እግዚአብሔር እኔ ነኝና፥ ስሜም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ሞገዱም እንዲተምም ባሕርን የማናውጥ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፥ ስሜም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። See the chapter |