ኢሳይያስ 50:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፤ የሚከራከረኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 የሚያጸድቀኝ በአጠገቤ አለ፤ ታዲያ ማን ሊከስሰኝ ይችላል? እስኪ ፊት ለፊት እንጋጠም! ተቃዋሚዬስ ማን ነው? እስኪ ይምጣ! See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 የሚፈርድልኝ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ ታዲያ ማን ይከሰኛል? የሚከሰኝ ካለ ፊት ለፊት እንገናኝ፤ እስቲ ይቋቋመኝ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? እስቲ በእኔ ላይ ይነሣ፤ የሚከራከረኝስ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፥ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፥ የሚከራከረኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ። See the chapter |