ኢሳይያስ 49:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የተሰሩትንም፦ ‘ውጡ’ በጨለማም የተቀመጡትን፦ ‘ተገለጡ’ እንድትል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ። በመንገድም ላይ ይሰማራሉ፥ ማሰማርያቸውም በገላጣ ኮረብታ ሁሉ ላይ ይሆናል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የተማረኩትን፣ ‘ኑ ውጡ’ በጨለማ ያሉትን፣ ‘ነጻ ሁኑ!’ እንድትል አድርጌሃለሁ። “በየመንገዱ ዳር ይመገባሉ፤ በተራቈተውም ኰረብታ ሁሉ ላይ መሰማሪያ ያገኛሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 አንተም እስረኞችን ‘በነጻ ሂዱ!’ በጨለማ ያሉትን ‘ወደ ብርሃን ውጡ’ ትላቸዋለህ፤ በየመንገዱ ምግብ ያገኛሉ፤ ደረቅ በነበረውም ተራራ ላይ እንደ ፍየል ይሰማራሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የተጋዙትንም፦ ውጡ፤ በጨለማም የተቀመጡትን፦ ተገለጡ፤ ትል ዘንድ።” በመንገድም ሁሉ ላይ ይሰማራሉ፤ ማሰማሪያቸውም በጥርጊያ ጎዳና ሁሉ ላይ ይሆናል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የተጋዙትንም፦ ውጡ በጨለማም የተቀመጡትን፦ ተገለጡ ትል ዘንድ ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ። በመንገድም ላይ ይሰማራሉ፥ ማሰማርያቸውም በወና ኮረብታ ሁሉ ላይ ይሆናል። See the chapter |