ኢሳይያስ 49:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 እኔ ግን፦ “በከንቱ ደከምሁ፥ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጉልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ ግን በጌታ ዘንድ፥ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልኩ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እኔ ግን፣ “ዐላማ ሳይኖረኝ እንዲሁ ደከምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ነገር ጕልበቴን ጨረስሁ፤ ሆኖም ግን ብድራቴ በእግዚአብሔር እጅ፣ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እኔ ግን “በከንቱ ለፋሁ፤ ያለ ጥቅም በከንቱ ጒልበቴን አባከንሁ፤ ሆኖም ጉዳዬ በእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ የድካሜም ዋጋ ከአምላኬ ጋር ነው” አልኩ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እኔ ግን፥ “በከንቱ ደከምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጕልበቴን ፈጀሁ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ይፈርድልኛል፤ መከራዬም በአምላኬ ፊት ነው” አልሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እኔ ግን፦ በከንቱ ደከምሁ፥ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጕልበቴን ፈጀሁ፥ ፍርዴ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ፥ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው አልሁ። See the chapter |