ኢሳይያስ 49:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ባድማሽና ውድማሽ ወናም የሆነው ምድርሽ ከሚኖሩብሽ የተነሣ ዛሬ ጠባብ ትሆናለችና፥ የዋጡሽም ይርቃሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 “ፈራርሰሽ ባድማ ብትሆኚ፣ ምድርሽ ፈጽሞ ቢጠፋ፣ ዛሬ ለሕዝብሽ ጠባብ ብትሆኚም እንኳ፣ የዋጡሽ ከአንቺ ይርቃሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “ ‘ፈራርሰሽ ባድማ እንድትሆኚ፥ ምድርሽም ጠፍ እንዲሆን ቢያደርጉሽም እንኳ፥ አሁን አንቺ ተመልሰው ለሚመጡ ለነዋሪዎችሽ ጠባብ ትሆኚአለሽ፤ የአፈራረሱሽም ከአንቺ ርቀው ይሄዳሉ።’ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ፈርሰሻልና፥ ፈጽመሽም ጠፍተሻልና በአንቺ ለሚኖሩ ሰዎች ዛሬ ጠባብ ትሆኚባቸዋለሽ፤ ያጠፉሽም ከአንቺ ይርቃሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ባድማሽና ውድማሽ ወናም የሆነው ምድርሽ ከሚኖሩብሽ የተነሣ ዛሬ ጠባብ ትሆናለችና፥ የዋጡሽም ይርቃሉና። See the chapter |