ኢሳይያስ 48:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ስለዚህ፥ አንተ፦ “ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፥ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌ ይህን አዘዙኝ” እንዳትል፥ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር፥ ከመሆኑም በፊት አሳይቼህ ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ገና ድሮ ነገርሁህ፤ ከመፈጸማቸው በፊት አስታወቅሁህ፤ ይህም፣ ‘ጣዖቶቼ ይህን አደረጉ፤ ከዕንጨት የተቀረጸው ምስልና ከብረት የተሠራው አምላኬ ይህን ወስኗል’ እንዳትል ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፤ ከመፈጸማቸውም በፊት አስታውቄአችኋለሁ፤ ይህንንም ያደረግኹት ‘ጣዖቶቻችን ይህን አደረጉ፤ የእንጨትና የብረት ምስሎቻችን ይህን ወሰኑ’ እንዳትሉ ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ስለዚህ፥ አንተ፥ “ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፤ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌም ይህን አዘዙኝ” እንዳትል፥ የሚሆነውን ከመሆኑ በፊት ነገርሁህ፤ አስረዳሁህም፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ስለዚህ፥ አንተ፦ ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፥ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌ ይህን አዘዙኝ እንዳትል፥ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር ሳይሆንም አሳይቼህ ነበር። See the chapter |