Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 44:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አመድ ይበላል፥ የተታለለ ልብ አስቶታል፥ ነፍሱን ለማዳን አይችልም፥ ወይም፦ “በቀኝ እጄ ሐሰት አለ?” ብሎም አይጠይቅም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ዐመድ ይቅማል፤ ተታላይ ልብ አስቶታል፤ ራሱን ለማዳን አይችልም፤ “ይህ በቀኝ እጄ ያለው ነገር ሐሰት አይደለምን?” ለማለት አልቻለም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ተቃጥሎ ዐመድ የሚሆነውን እንጨት እስከ ማምለክ ድረስ ሰው እንዴት ሞኝ ይሆናል? የሞኝነት አስተሳሰቡ አሳስቶታል፤ ራሱን ማዳን አይችልም፤ ወይም “ይህ በቀኝ እጄ ያለው ነገር ጣዖት እንጂ አምላክ አይደለም።” ብሎ መናገር አይችልም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እን​ግ​ዲህ ልባ​ቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነፍ​ሱን ለማ​ዳን የሚ​ችል ማንም እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚ​ልም እን​ደ​ሌለ ተመ​ል​ከቱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አመድ ይበላል፥ የተታለለ ልብ አስቶታል፥ ነፍሱን ለማዳን አይችልም፥ ወይም፦ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ አይልም።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 44:20
29 Cross References  

እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ እግዚአብሔር ተገቢ ያልሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤


ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፤ ይሁዳ ግን እስካሁንም ከጌታ ጋር ይመላለሳል ለቅዱሱም ታማኝ ነው።


ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም በእኔ ስም ይራገማሉ።


ራሱን እያሳተ በከንቱ ነገር አይታመን ዋጋው ከንቱ ነገር ይሆናልና።


እኛ ታማኝ ባንሆን፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።”


የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ለወጡ፤ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡርን አመለኩ አገለገሉትም፤ እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም የተባረከ ነው፤ አሜን።


የዝሙት መንፈስ አስቶአቸዋልና፥ እነርሱም ከአምላካቸው ርቀው አመንዝረዋልና ሕዝቤ ግዑዝ እንጨታቸውን ይጠይቃሉ፥ በትራቸውም ይመልስላቸዋል።


ሺህ ዓመትም አሰረው፤ ወደ ጥልቅም ጣለው፤ አሕዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም አደረገበት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ መፈታት ይገባዋል።


የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”


በአውሬውም ፊት እንዲያደርግ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቁስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲሠሩ በምድር የሚኖሩትን ያዛቸዋል።


ታላቁም ዘንዶ ወደ ታች ተጣለ፤ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።


ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አስመሳዮች እያታለሉና እየተታለሉ ከክፋት ወደ ባሰ ክፋት ይሄዳሉ።


ይህም ትምህርት ኅሊናቸውን በጋለ ብረት በማቃጠል አደንዝዘው ውሸትን በሚናገሩ ግብዞች በኩል የሚሰጥ ነው፤


ዐሣማዎችም ከሚበሉት ፍልፋይ ለመጥገብ ይመኝ ነበር፤ የሚሰጠውም አልነበረም።


ሠሪው የቀረጸውና ቀልጦ የተሠራ ምስል የውሸት አስተማሪ ነውና፤ ዲዳ ጣዖትን በመሥራት ሠሪው በሠራው ይታመናልና፤ የተቀረጸ ምስል ምን ይጠቅማል?


አቤቱ! ኃይሌ፥ አምባዬ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ፥ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር የማይረባቸውንም ወርሰዋል፤


ዐምፀናል፥ ሐሰትን ተናግረናል፥ ጌታን ከመከተል ተመልሰናል፤ ግፍንና ዓመፅንም ተናግረናል፥ የኃጢአት ቃልንም ፀንሰን ከልብ አውጥተናል።


የአዋቂ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፥ የሰነፎች አፍ ግን በስንፍና ይሰማራል።


“በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ነፋስ በሆነ እውቀት ይመልሳልን? ሆዱንስ በምሥራቅ ነፋስ ይሞላልን?


የአሕዛብ ጣዖታቶች የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።


አድነኝ፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥ ቀኛቸውም የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ።


በክፋትሽ ታምነሻል፤ “የሚያየኝ የለም” ብለሻል፤ ጥበብሽና እውቀትሽ አታልለውሻል፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ብለሻል።


ሐሰትን የተናገርሺው እኔንም ያላሰብሽው፥ በልብሽም ነገሩን ያላኖርሺው፥ ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔ ብዙ ጊዜ ዝም አልሁ፥ አንቺም አልፈራሽም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements