ኢሳይያስ 44:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ጠራቢው ገመድ ይዘረጋል፥ በጠመኔም ምልክት ያኖራል፥ በመሮም ይቀርጸዋል፥ በመለኪያም ይለከዋል፤ በቤትም ውስጥ እንዲቀመጥ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ይቀርጸዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 የእጅ ጥበብ ባለሙያ በገመድ ይለካል፤ በጠመኔ ንድፍ ያወጣል፤ በመሮ ይቀርጸዋል፤ በጸርከል ምልክት ያደርግበታል። በሰው አምሳል ይቀርጸዋል፤ የሰውንም ውበት ያለብሰዋል፤ በማምለኪያም ስፍራ ያስቀምጠዋል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 አናጢ በእንጨቱ ላይ መስመርን ያሰምራል፤ ንድፍም ይነድፋል፤ በመላጊያ ያለሰልሰዋል፤ በማስተካከያ መሣሪያም ትክክልነቱን ያረጋግጣል፤ ውበት ያለው የሰው ቅርጽ እንዲኖረው ያደርጋል። ከዚያም በጣዖት ቤት ያኖረዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ጠራቢውም እንጨት ቈርጦ በልኩ ያቆመዋል፤ በማጣበቂያም ያያይዘዋል፤ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ያስመስለዋል፤ በቤትም ውስጥ ያቆመዋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ጠራቢውም ገመድ ይዘረጋል በበረቅም ያመለክተዋል በመቅረጫም ይቀርጸዋል በመለኪያም ይለከዋል፥ በቤትም ውስጥ ይቀመጥ ዘንድ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ያስመስለዋል። See the chapter |