ኢሳይያስ 44:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ብረት ሠሪ መጥረቢያውን ይሠራል፥ በፍምም ውስጥ ያደርገዋል፥ በመዶሻም መትቶ ቅርጽ ይሠጠዋል፤ በክንዱም ኃይል ይሠራዋል፥ እርሱም ይርበዋል ይደክማልም፤ ውኃም ለመጠጣት ይታክታል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 የብረት የእጅ ጥበብ ባለሙያ መሥሪያን ይይዛል፤ በከሰል ፍም ላይ ይሠራዋል፤ ጣዖትን በመዶሻ ቅርጽ ይሰጠዋል፤ በክንዱም ኀይል ያበጀዋል። ከዚያም ይራባል፤ ጕልበት ያጣል፤ ውሃ ይጠማል፤ ይደክማል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 አንጥረኛ ጣዖትን ለመሥራት ብረትን ወስዶ በእሳት ያቀልጠዋል። ለብረቱም ቅርጽ ለመስጠት በብርቱ ክንዱ በመዶሻ ይቀጠቅጠዋል፤ ይህንንም በሚሠራበት ጊዜ ይራባል፥ ይጠማል፥ ይደክማልም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ብረት ሠሪ መጥረቢያውን ይስላል፤ ጣዖቱን በመጥረቢያ ይቀርጸዋል፤ በመዶሻም መትቶ ቅርጽ ይሰጠዋል፤ በክንዱም ኀይል ይሠራዋል፤ እርሱም ይራባል፤ ይደክምማል፤ ውኃም አይጠጣም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ብረት ሠሪ መጥረቢያውን ይሠራል፥ በፍምም ውስጥ ያደርገዋል፥ በመዶሻም መትቶ ቅርጽ ይሠጠዋል፥ በክንዱም ኃይል ይሠራዋል፥ እርሱም ይራባል ይደክምማል፥ ውኃም አይጠጣም ይታክትማል። See the chapter |