ኢሳይያስ 42:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ከአገልጋዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹም ተገዢዬ ወይም እንደ ጌታ አገልጋይ ዕውር የሆነ ማን ነው? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 አገልጋዬ እንጂ፣ ሌላ ዕውር ማን አለ? ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ማን ደንቈሮ አለ? ለእኔ ታማኝ እንደ ሆነ ሰው የታወረ፣ እንደ እግዚአብሔርስ አገልጋይ ዕውር ማነው? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ከአገልጋዬ በቀር ዕውር ማነው? ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ ማነው? ራሱን ለእኔ እንዳስገዛው ያለው ዕውር ማን ነው? ወይም እንደ እግዚአብሔር አገልጋይ ያለ ዕውር ማን ነው? See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ከባሪያዎች በቀር ዕውር ማን ነው? ከአለቆቻቸውስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? የእግዚአብሔር ባሪያዎች ታወሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹሙ ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው? See the chapter |