Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 41:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እነሆ፥ እንዳልነበረ ናችሁ፥ ሥራችሁም ከንቱ ነው፤ የሚመርጣችሁም አስጸያፊ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እነሆ፤ እናንተ ከምንም የማትቈጠሩ ናችሁ፤ ሥራችሁ ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ነው፤ የመረጣችሁም አስጸያፊ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እናንተም ሆናችሁ ድርጊታችሁ በእርግጥ ከንቱ ነው፤ እናንተን ማምለክ የሚሹም አጸያፊዎች ናቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እና​ንተ ከየት ናችሁ? ከየ​ትስ ሠሯ​ችሁ? ከም​ድር የሚ​መ​ር​ጧ​ች​ሁም የረ​ከሱ አይ​ደ​ሉ​ምን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እነሆ፥ እንዳልነበረ ናችሁ፥ ሥራችሁም ከንቱ ነው፥ የሚመርጣችሁም አስጸያፊ ነው።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 41:24
17 Cross References  

እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት፥ ጣዖት በዓለም ከንቱ እንደ ሆነና ከአንዱ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።


የሚሠሩአቸው፥ የሚያምኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።


እነሆ፥ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ ሥራቸውም ምንም ናት፤ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ባዶ ነፋስ ናቸው።


በአንድ ጊዜ ቂላ ቂሎችና ሞኞች ሆነዋል፤ ጣዖታት የሚያስተምሩት ከግዑዝ እንጨት የማይሻልን ነገር ብቻ ነው።


በግምባርዋም “ታላቂቱ ባቢሎን፥ የአመንዝሮችና የምድር ርኩሰት እናት” የሚል ምስጢራዊ የሆነ ስም ተጻፈ።


ሰው ሁሉ ቂላ ቂልና እውቀት የሌለው ሆኖአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።


ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።


አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ፥ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።


“‘በጌታ ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


እንደ እርሱም ለጥፋት የምትሆን እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።


ጠማማ ሁሉ በጌታ ፊት ርኩስ ነውና፥ ወዳጅነቱ ግን ከቅኖች ጋር ነው።


ሕግን ከመስማት ጆሮውን የሚመልስ ጸሎቱ እንኳን ሳይቀር አስጸያፊ ናት።


በዱባ እርሻ (የአትክልት ስፍራ) ውስጥ እንዳለ እንደ ወፍ ማስፈራርያ ዓምድ ናቸው፥ እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም ስለማይችሉ ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራት አይችሉምና፥ ደግሞም መልካም መሥራት በእነርሱ ውስጥ የለምና አትፍሩአቸው።”


እነርሱ ምናምንቴና የቀልድ ሥራ ናቸው፤ በተጐበኙ ጊዜ ይጠፋሉ።


የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ አትመኝ፥ በጌታ አምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements