ኢሳይያስ 41:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 በምድረ በዳ፤ ዝግባን፤ ግራርን፤ ባርሰነትንና ወይራን አበቅላለሁ፤ በበረሃ፤ ጥድን፤ አስታንና ሸውሸዌን በአንድነት እተክላለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 በምድረ በዳ፣ ዝግባን፣ ግራርን፣ ባርሰነትንና ወይራን አበቅላለሁ፤ በበረሓ፣ ጥድን፣ አስታንና ሸውሸዌን በአንድነት እተክላለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 የሊባኖስ ዛፎችን፥ የግራር እንጨቶችን፥ ባርሰነቱንና የወይራ ዛፎችን በበረሓ አበቅላለሁ፤ በምድረ በዳ ዝግባ፥ አስታና ጥድ፥ ወይራ የሞላበት ደን አበቅላለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 በምድረ በዳ ዝግባውንና ግራሩን፥ ባርሰነቱንና የዘይቱን ዛፍ አበቅላለሁ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19-20 የእግዚዘብሔር እጅ ይህን እንደ ሠራች፥ የእስራኤልም ቅዱስ እንደ ፈጠረው ያዩ ዘንድ ያውቁም ዘንድ ያስቡም ዘንድ በአንድነትም ያስተውሉ ዘንድ፥ በምድረ በዳ ዝግባውንና ግራሩን ባርሰነቱንና የዘይቱን ዛፍ አበቅላለሁ፥ በበረሃውም ጥዱንና አስታውን ወይራውንም በአንድነት አኖራለሁ። See the chapter |