Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢሳይያስ 41:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እነሆ፥ እንደ ተሳለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ፤ ተራሮችንም ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ፥ ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “እነሆ፣ አዲስ የተሳለና ባለጥርስ ማሄጃ አደርግሃለሁ፤ ተራሮችን ታሄዳለህ፤ ታደቅቃቸዋለህ፤ ኰረብቶችንም ገለባ ታደርጋቸዋለህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እነሆ፥ እኔ እንደ ስለታም፥ አዲስና፥ ጥርስ እንዳለው የመውቂያ መሣሪያ አደርግሃለሁ፤ ተራራዎችንም በማበራየት ታደቃቸዋለህ፤ ኰረብቶችንም ዳምጠህ እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እነሆ፥ እንደ ተሳ​ለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም ታሄ​ዳ​ለህ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም ታደ​ቅ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ እንደ ገለ​ባም ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እነሆ፥ እንደ ተሳለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ፥ ተራሮችንም ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ፥ ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።

See the chapter Copy




ኢሳይያስ 41:15
20 Cross References  

የጽዮን ልጅ ሆይ ተነሺ አሂጂ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ኮቴሽንም ናስ አደርጋለሁና፤ ብዙ ሕዝቦችን ታደቅቂአለሽ፤ እኔም ትርፋቸውን ለጌታ፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ አውለዋለሁ።


ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎችም፦ ‘ሞገስ ይሁንለት! ሞገስ ይሁንለት!’ ብለው እየጮኹ እርሱ የመደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል” ብሎ ነገረኝ።


በቁጣ ምድርን ረገጥሃት፥ አሕዛብን በንዴት አሄድሃቸው።


እናንተ በአውድማዬ ላይ የተወቃችሁ የአውድማዬ ልጆች ሆይ፥ ከእስራኤል አምላክ ከሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሰማሁትን ነገርኳችሁ።


ጥቁሩ አዝሙድ በመውቂያ አይወቃም፥ ከሙንም የሠረገላ መንኰራኵር አይዞርበትም፤ ነገር ግን ጥቁሩ አዝሙድ በሽመል ከሙኑም በበትር ይወቃል።


ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፥ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ነገር ግን አልመለሰላችውም።


ሕዝቦች እንደ ብዙ ውኃ ጩኸት ይጮኻሉ፤ እርሱ ግን ይገሥጻቸዋል፤ እነርሱም እየሸሹ ይርቃሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ በነፋስ ፊት፥ ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረውም ትቢያ ይበተናሉ።


ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል።


ተራሮችንና ኮረብቶችን አፈርሳለሁ፥ ቡቃያዎቻቸውንም ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ደሴቶች አደርጋለሁ፥ ኩሬዎችንም አደርቃለሁ።


ምነው ሰማያትን ቀደህ ብትወርድ! ምነው ተራሮችም ቢናወጡ!


“ለተራሮች ልቅሶንና እንጉርጉሮን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው ባድማ ሆነዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፤ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።


አንቺ መዶሻዬና የጦር መሣሪያዬ ነሽ፤ በአንቺ አሕዛብን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም መንግሥታትን አጠፋለሁ፤


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ ዐውድማ ነች፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።”


ምድሪቱን ባድማና ውድማ አደርጋታለሁ፥ የኃይልዋም ትዕቢት ይቀራል፥ የእስራኤልም ተራሮች ማንም እንዳያልፍባቸው ባድማ ይሆናሉ።


እጅህ በጠላቶችህ ላይ ትነሣለች፥ ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ።


ነገር ግን ተራራማው አገር ለአንተ ይሆናል፥ ዱር እንኳን ቢሆንም ትመነጥረዋለህ፥ ለአንተም ይሆናል፤ ለከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ቢኖሩአቸው የበረቱም ቢሆኑ ታሳድዳቸዋለህ።”


ጌታም፥ “በእርግጥ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ምድያማውያንንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታቸዋለህ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements